ዶ/ር ምህረት ደበበ በሙያው የአእምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት ነው፡፡ የሕክምና ዲግሪውን የሠራው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሲሆን በኋላም አሜሪካ ሀገር ሄዶ በሴይንት ሊዊስ ዩኒቨርስቲ የአእምሮ ሕክምና ጥናቱን አጠናቀቀ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በአሜሪካና በኢትዮጵያ መካከል እየተመላለሰ በሁለቱም ስፍራ በሙያው በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ ከሕክምው በተጨማሪ በአስተሳሰብ እና የአእምሮ ለውጥ ዙሪያ ማሰብ፣ ማጥናት እና ማስተማር ያዘወትራል፡፡
እስካሁንም ሁለት መድብሎችን በ2005ዓ.ም እና በ2007ዓ.ም "የተቆለፈበት ቁልፍ" እና "ሌላሠው" በሚሉ ርዕሶች አቅርቦልናል::

